SwePub
Tyck till om SwePub Sök här!
Sök i LIBRIS databas

  Extended search

db:Swepub
 

Search: db:Swepub > Amharic > Ethiopia :

  • 1 of 1
  • Previous record
  • Next record
  •    To hitlist

Ethiopia : Reflections on Media Reform

Fojo Media Institute, . (author)
FOJO
ተወልደ, ሚኪ (photographer)
አማኑኤል, ኢዛት (creator_code:cov_t)
show more...
ጌታነህ, ቢንያም (translator)
Nubia Media and Communications, . (contributor)
show less...
 (creator_code:org_t)
Kalmar, sweden : Fojo Media Institution, 2019
Amharic 63 s.
  • Reports (pop. science, debate, etc.)
Abstract Subject headings
Close  
  • የአርታዒ መልዕክት እና ምስጋናርዕሱ እንደሚያመለክተው ይህ መጽሔት ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና በለውጥ ጊዜ ስላለ የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ዙሪያ ዕውቀት ለመጨበጥ ለሚሹ ማንኛውም ሰው ወሳኝ አስተያየቶችን እና ጠቃሚ ነጥቦችን ለመጠቆም የተዘጋጀ ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካዊ አርታዒ ስሆን አብዛኛውን የሕይወት ጊዜዋን የአፍሪካ ጉዳይ ዘጋቢ በመሆን በጋዜጠኝነት ልምድ ያላት እና እ.ኤ.አ ከመስከረም 2018 ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት በፎዮ ሚዲያ ኢንስቲትዩት የተመደበችው ግሩም ልምድ ያላት የስዊድን ጋዜጠኛ ማሪካ ግሪሼል ይህንን መጽሔት እንዳርም ተመድቤ ነበር፡፡ማሪካ ከኑቢያ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ፡ በፕሬስ ነፃነት ፣ ራስ ገዝ አስተዳደር ፣ የመገናኛ ብዙሃን ቢዝነስ ሞዴሎች ፣ የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት እንዲሁም የስነ-ፆታ በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ውክልና ዙሪያ የተለያዩ ሴሚናሮችን አዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህ ሴሚናሮች ሚያዝያ 1 -2 ፣ 2011 በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) በተዘጋጀ እና “ጋዜጠንነትን እና ዴሞክራሲን በተግባር - የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ በለውጥ ጊዜ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ስኬታማ ኮንፈረንስ ተጠናቀዋል፡፡የዚህ መጽሔት ይዘት እና የጸሐፊዎቹ ስብስብ ቅንጅት የተጀመረው እ.ኤ.አ በየካቲት 2019 መጀመሪያ አካባቢ በአንድ ሆቴል የቦርድ ክፍል ውስጥ በብዙ የኢትዮጵያ ቡና ብርታት ሰጪነት በነበረ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህ መጽሔት ይህን ቅርፅ እንዲይዝ የተሳተፉት የኑቢያ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ሀድራ አህመድ ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ ንጉሱ ሶሎሞን ፣ የስነ-ፆታ ባለሞያዋ ሰላም ሙሴ ፣ ማሪካ ግሪሼል እና እኔ ነበርን፡፡ ስለዚህ የዚህ መጽሔት ጅማሮ የሶስት ሀገር ዜጎች የኢትዮጵያ ፣ ስዊድን እና ደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኞች የቡድን ጥረት ነበር፡፡ በዚህ መጽሔት ላይ በመፃፍ የተሳተፉት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም እንደ ዚምባብዌ ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ካሉ ሃገራት የመጡ ጋዜጠኞች እና ባለሞያዎች እንዲሁም ከአህጉራችን ውጪ የተሳተፉ ጥቂት ፀሐፍያን ሲኖሩ መጽሔቱ ዓለም አፍሪካዊ መነሻ ኖሮት አለም አቀፋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጉታል፡፡ይህ መጽሔት ዕውን እንዲሆን የረዱ የተወሰኑ ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን ማመስገን እሻለሁ፡፡ ላርስ ታለርት ፣ ማሪካ ግሪሼል እና ታታሪውን የፎዮ ቡድን ፣ ለትርፍ ባልቆመው ሊናስ ዩኒቨርሲቲ የሚደገፈውን የስዊድን መገናኛ ብዙሃን እድገት ኢንስቲትዩት ማመስገን እሻለሁ፡፡ አኔት እና የአዲስ አበባ ስዊድን ኤምባሲ ሰራተኞችን ፤ የ ኑቢያ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽኖቹ ሀድራ አህመድ ፣ ንጉሱ ሶሎሞን እና ሰላም ሙሴ ፤ መፅሔቱ ውስት ያሉትን ፎቶዎች ያነሳልን ሚኪ ተወልደ ፤ መጽሔቱን በሚያምር ዲዛይኑ ያስዋበልን ኢዛት አማኑኤል ፤ እንግሊዝኛ ፅሁፎችን ወደ አማርኛ የተረጎመልን ቢንያም ጌታነህ ፤ በመጨረሻም ለዚህ መጽሔት ስኬት ጠንክረው ሲሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞችን እና ፀሐፊዎችን አመሰግናለሁ፡፡                                  የናንተው - የመረጃ ፍሰትን ነፃ ከማድረግ ጋር                                                   ሄዘር ሮበርትሰን                                               ሚያዝያ 6 2011 ዓ.ም.

Subject headings

SAMHÄLLSVETENSKAP  -- Medie- och kommunikationsvetenskap (hsv//swe)
SOCIAL SCIENCES  -- Media and Communications (hsv//eng)

Keyword

Medievetenskap och journalistik
Media Studies and Journalism
Media and Communication Science
Medie- och kommunikationsvetenskap

Publication and Content Type

pop (subject category)
rap (subject category)

To the university's database

  • 1 of 1
  • Previous record
  • Next record
  •    To hitlist

Search outside SwePub

Kungliga biblioteket hanterar dina personuppgifter i enlighet med EU:s dataskyddsförordning (2018), GDPR. Läs mer om hur det funkar här.
Så här hanterar KB dina uppgifter vid användning av denna tjänst.

 
pil uppåt Close

Copy and save the link in order to return to this view